ሊቀ ማዕምራን መምህር ዶክተር ዘበነ ለማ እንኳን ደስ አለዎት!!!
የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደሪ … በዕውቀት፣ በማዕረግ … ከፍ ብለውልናል ። ከሐዋርድ ዩኒቨርስቲ 2ኛ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ይህ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ግብአት ያለው ውጤታማነት ነው። አኩሪ ስራ ነው።
በመሆኑም hደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፣ አስተዳደርና ካህናት በሙሉ ከፍተኛ ደስታችን ነው።
እንኳን ደስ አለዎት። እንኳን ደስ አለን።
ሊቀ ማዕምራን መምሕር ዶ/ር ዘበነ ለማ –
በአሜሪካን ሀገር፣ በዋሽንግቶን ዲሲ ሜትሮ አካባቢ፣ በቴምፕል ሂል ሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አለቃ ናቸው ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግቶን ዲ.ሲ. ሜትሮና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትመካባቸው ድንቅ የወንጌል ገበሬ ናቸው። በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ከሚሰሩት ሰፊ የሆነ የወንጌልና የቤተ ክርስቲያን ማስፋፋት ስራ ባሻገር፣ በሰሜን አሜሪካ በአውሮፓ በቅርብ ምሥራቅ በጠቅላላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱን የወንጌል ዘር በመዝራት ወደር የሌለው ሥራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ሁለት መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅተዋል። አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራት ምዕመናን ገንዘባቸውን እንዲያዋጡ በተሰጣቸው መክሊት እያስተባበሩ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን በማሰራት ከፍተኛ የሆነ ሥራ አከናውነዋል።
በወገን ላይ የሚደርሱ ሰዉ ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመርዳት ብዙ ገንዘብ እያሰባሰቡ አንጋፋ ተዋጽኦ በማበርክት ላይ ይገኛሉ።
በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች፣ ለጣና ፣ ለዋልድባ ፣ ለሊቢያ ጉዳተኞች እርዳታ …ወዘተ በማሰባሰብ ከፍተኛ ሥራ ያበረክታሉ።
ለሁለተኛ ጊዜ የዶክትሬት ዲግሪ ሲቀበሉ ካሉት ላይቀር ፍሬ ማፍራት ከፍ ብሎ መገኘት እንዲህ ነው እንድንል ከርሳቸው ጥረትና ፍሬ ማፍራት አንድንማር ኣርኣያ ሆነውናል ።
መንፈሳዊ አባታችን፣ ወንድማችን መምሕር ዶክተር ዘበነ ለማ እንኳን ደስ አለዎት!!!
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘላለም ትኑር!!!